ዘመነኛ የሸሪዓ ሕግ እድገቶች፡- ከኢትዮጵያዊ ምልከታዎች ጋር

Authors

  • አልዩ አባተ ይማም

Keywords:

የሕግ ብዝኃነት, ሸሪዓ, ፊቅሕ, ኢጅቲሓድ, የሕግ ምርምር, ሙጅተሒድ, ዘመነኛ እድገቶች

Abstract

One of the main manifestations in the pluralistic aspect of the Ethiopian legal system is the adjudication of disputes arising from personal and family relationships in accordance with sharia law. Sharia courts of the country have a long existence in the country’s justice alongside regular courts for over half a century. The personal and family laws of Sharia as well as its general legal framework has been developed by two legal disciplines of Islam i.e. Usul al-Fiqh (Islamic Jurisprudence) and Fiqh (Islamic law). These two fields of law are developed by the schools of law (Madhahib) of Sharia that have been evolving and contributing since the formative periods of Sharia law. Since the late 19th century, a wave of contemporary Sharia jurists have arisen across the world bringing new insights to the Sharia jurisprudence, besides the intellectual legacy of Madhhabs for fourteen centuries. As a response to the long entrenched problem of blind following of Madhhabs (Taqlid) and the coming into decay of original thought in the intellectual and legal tradition of the Muslim civilization, the modern day jurists and leaders of Muslim communities have introduced various educational and structural reforms to the understanding and application of Sharia law in the modern period. Such reforms include the compilation of Fiqh Encyclopedias which made access to the widely dispersed corpus of Fiqh ruling cross Madhahib’s legal literature. Further, the 19th and 20th century reform movements have brought about the establishment of national and international Islamic Law Academies which have engaged in pronouncing rulings on the most controversial Fiqh issues of the time. The content and approach to the study of Sharia law has been advanced in a way that nourish fresh jurisprudential thought. This has contributed to the unified interpretation of Sharia law in Muslim communities across the world. Such new developments in the discourse of Sharia law would provide a good example for national jurisdictions like Ethiopia where application of Islamic law needs to be informed by the prevailing national and local realities.

 

አህጽሮተ-ጽሑፍ

የኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓት የብዝኃነት አይነተኛ መገለጫዎች መካከል አንዱና ዋነኛው ሸሪዓ ፍ/ቤቶች ከመደበኛው የፍትሕ ሥርዓት በተጓዳኝ የግልና የቤተሰብ ግጭቶችን በሸሪዓ ሕግ አማካይነት እልባት እየሰጡ መገኘታቸው ነው፡፡ የሸሪዓ ሕግ ሲባል ሁለት መሠረታዊ ክፍሎችን ሊወክል ይችላል፤ እነሱም የሕግ መርሆዎች (ኡሱል አል-ፊቅሕ) እና ዝርዝር ሕግጋት (ፊቅሕ) ናቸው፡፡ ጠቅላላ የሸሪዓ የሕግ መርሆችንና ዝርዝር የግልና የቤተሰብ ሕጎችን በማዳበር ረገድ፣ ጥንታዊ አነሳስ ያላቸው የሱኒ እና የሺዓ የሕግ ት/ቤቶች ቀዳሚና ሰፊ ድርሻ አላቸው፡፡ ከ19ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ማብቂያ በኋላ የተነሱ የቅርብ ዘመን የሸሪዓ ምኁራን ደግሞ የቀደመውን የሕግ እውቀት አሻራ ተቀብለው ሸሪዓ የዘመኑን ሙስሊም ማሕበረሰብ ተጨባጭ እውነታዎች መሠረት ያደረገ ቅርጽ እንዲኖረው፣ ለሚነሱ አዳዲስ የሕግ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጥና ችግር ፈቺ መሆን ይችል ዘንድ፣ በነባሩ የሸሪዓ ፍልስፍናዎችና ዝርዝር ሕጎች ላይ ምርምር (ኢጀቲሓድ) በማድረግና አዲስ ምልከታዎችን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በቀደመው የሙስሊሙ ዓለም ሥነ-እውቀታዊ ባህል ውስጥ ሥር ሰዶ እሰካለንበት ዘመን ድረስ የዘለቀውን የጭፍን ተከታይነት (ተቅሊድ) እና የሕግ እሳቤ ትምህርት ቤቶችን ወገንተኝነት ችግር በዓለም-አቀፉ የሙስሊም ሥልጣኔ ላይ የደረሰ ትልቅ ቀውስ መሆኑን በመገንዘብ ይህን ችግር ለመቅረፍ ተቋማዊ እና የተቀናጀ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህም ጥረቶች መካከል፣ ተደራሽነታቸውን ለማረጋገጥና ቡድናዊ የእሳቤ ውስንነትን ለመቅረፍ ይቻል ዘንድ በተለያዩ የሕግ ት/ቤቶች እና ሊቃውንት ድርሳናት ውስጥ ተበታትኖ የሚገኘውን ሽሪዓዊ የሕግ ብይኖች ማጠናቀር፣ የሸሪዓን ተገማችነት ለማረጋገጥ እንዲሁም የጋራ የሸሪዓ አረዳድ እና አፈጻጸም ሊያዝባቸው በሚገቡ፣ እና የብዙሓኑን አማኝ ማህበረሰብ በሚያወዛግቡ ጭብጦች ላይ ወጥ ብይን ማሰተላለፍ ይቻል ዘንድ ብቁ የሸሪዓ ሊቃውንት ያቀፉ ምክር-ቤቶችን በሃገር፣ በክፍለ-አህጉር እና በዓለም-አቀፍ ደረጃ በማደራጀት፣ ገለልተኛና ሳይንሳዊ የጥናት ዘዴን የሚከተሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አካል የሆኑ እንዲሁም ራሳቸውን የቻሉ የሸሪዓ ጥናት ማዕከላትና ተቋማትን ማቋቋም፣ ተጠቃሽ ዘመነኛ እድገቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ዓለም-አቀፍ የሸሪዓ ተሃድሶ ምሁራዊ ንቅናቄዎች፣ ሸሪዓ በፍ/ቤቶች እና በሃገራችን ሊቃውንትና ማህበረሰብ በሚተገበርበት አግባብ ውስጥ ሃገራዊ እውነታዎችና የአስተሳሰብና የሥልጣኔ ደረጃዎች ታሳቢ ያደረገ መሰል ሃገራዊ የሸሪዓ አረዳድ እና የአተገባበር ማሻሻያዎችን እውን ለማድረግ ትምህርት ሊወሰድባቸው የሚገቡ መልካም ተሞክሮዎች ናቸው፡፡

Published

2021-10-04

How to Cite

ይማም አ. . አ. . (2021). ዘመነኛ የሸሪዓ ሕግ እድገቶች፡- ከኢትዮጵያዊ ምልከታዎች ጋር. Hawassa University Journal of Law, 4. Retrieved from https://journals.hu.edu.et/hu-journals/index.php/hujl/article/view/235