በፍትሐ-ብሄር ጉዳዮች ክርክር ሂደት በፍ/ቤት የሚሰጡ ቀጠሮዎች ምክንያታቸውና የተከራካሪ ወገኖች አለመቅረብ የሚያስከትለው ውጤት በኢትዮጵያ የፍትሐብሄር ሥነ-ሥርዓት ሕግ፡- ሕጉና አተገባበሩ

Authors

  • ተዋቸዉ ሞላ

Keywords:

ቀጠሮ, የፍትሐብሄር ክርክር, ፍ/ቤት, የተከራካሪዎች በቀጠሮ አለመቅረብ, የኢትዮጵያ የፍትሐብሄር ሥነ-ሥርዓት ሕግ

Abstract

Obviously, when the aggrieved party pleads his/her case before courts, the later usually renders several adjournments to perform various tasks in a given case in which the non-appearance of parties has an adverse effect on their constitutional rights. From several years until now, there is divergence before courts in Ethiopia, over the purpose of adjournments and effect upon non-appearance of one or both parties in a civil suit. Therefore, this article aimed to clarify the disagreement between adjournments in terms of purpose and their effects upon non-appearance of one or both parties in Ethiopia. The doctrinal research type and qualitative method of study was followed. Accordingly, the author finds; first, to pass a valid judgment on a given case a civil bench is expected to render five types of adjournments with different function on each category. Second, as the court’s function on each adjournment category is different, the effect upon the absentee(s) party on each adjournment is also different. This includes losing the right to be heard in writting, leading to either ex-parte proceeding, striking-out or dismissal of the suit as well as losing the right to evidence a claim by submitting witnesses testimony. The author concludes the function of court on each adjournment and effects upon non-appearance of the party(s) are different. Consequently, courts should duly and diligently perform functions of each adjournment to avoid delay, injustice, and be restrained from passing arbitrary penalty upon the absentee(s) party.

አህጽሮት-ጽሑፍ

ዜጎች ፍትሕ ለማግኘት ቅሬታቸዉን ለመደበኛው ፍ/ቤት ሲያቀርቡ መደበኛዉ የግጭት አፈታት ሂደት የሚከተላቸው ሥነ-ሥርዓቶችን የማክበር ግዴታ አለባቸዉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አንደኛው ሥነ-ሥርዓት የቀጠሮ ጊዜ ማክበር ነው፡፡ ለብዙ ጊዜ በሀገራችን ፍ/ቤቶች በቀጠሮ አሰጣጥ እና ክንዋኔዎቻቸዉ እንዲሁም የተከራካሪዎቹ አለመቅርብ ስለሚኖረዉ ዉጤት አጨቃጫቂ ከመሆኑም በላይ በፍ/ቤቶችም ወጥነት የጎደለዉ ልምድ ሲስታዋል ቆይቷል፤ ይስተዋላልም፡፡ ይህ ደግሞ በዜጎች ሕገ-መንግሰታዊ መብቶች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያስከትላል፡፡ ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነዉ ይህ ችግር ሲሆን በፍትሐ-ብሄር ችሎት የፍ/ቤት ቀጠሮ ትርጉም እና ክንዋኔ እንዲሁም ከተከራካሪ ወገኖች አንዱ ወይም ሁለቱም ቀጠሮ አክብረው አለመገኘታቸው የሚያስከትለውን ውጤት ግልጽ በማድረግ በዜጎች ላይ የሚደርሰዉን አሉታዊ ተፅዕኖ መቅረፍ አስፈላጊነቱን በማመን ነዉ፡፡ ለዚህ ጽሁፍ ዝግጅት መጽሐፍትን፣ ሕግጋትንና የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ዉሳኔዎችን ጸሀፊዉ ዳስሷል፡፡ በዚህ ጥናት የመጀመሪያዉ ግኝት በሕግ ማዕቀፉ ፍ/ቤት በተያዘው የክስ ጉዳይ አስፈላጊውን ክንውን ለማድረግ አምስት አይነት ቀጠሮ ሊሰጥ እና በእያንዳንዱ ቀጠሮም የተለያየ ክንዉን እንደሚያደረግ ያሳያል፡፡ ሁለተኛዉ ዋና ግኝት ፍ/ቤት በተለያየ ቀጠሮ የሚከናወነዉ ተግባር መለያየቱን ተከትሎ ከተከራካሪዎች አንዱ ወይም ሁለቱ ባይቀርቡ ሊከተሉ የሚችሉት ውጤቶች የተለያዩ ናቸው ፡፡ እነዚህም የተከሳሽ የጽሑፍ መልስ የማቅረብ መብት መታለፍ፣ በሌሉበት የክሱ መሰማት መቀጠል፣ የመዝገብ መዝጋት፣ የክስ መዘጋት እና ማስረጃ የማሰማት መብት መታለፍ ናቸዉ፡፡ ሕጉ የፍ/ቤት ቀጠሮና ክንዋኔ እንዲሁም ባልቀረቡ ተከራካሪዎች ላይ የሚወሰደዉ እርምጃን በሚመለከቱ አንዳንድ ድንጋጌዎች ላይ ግልፅነት የጎደለዉ እና በቂ አለመሆኑ እንዲሁም በሕጉ እና በአተገባበሩ መካከል ልዩነት መኖሩ ሌላዉ ችግር ነዉ፡፡ ስለዚህ ፍ/ቤቶች ለፍትሕ ሲባል በያዙት ቀጠሮ የሚተገብሩት ክንዋኔና ባልቀረቡ ተከራካሪዎች ላይ የሚከተለዉ ዉጤት የሕጉ ዓላማና ይዘትን መሠረት ያደረገ መሆን አለበት፡፡

Downloads

Published

2022-01-17

How to Cite

ተዋቸዉ ሞላ. (2022). በፍትሐ-ብሄር ጉዳዮች ክርክር ሂደት በፍ/ቤት የሚሰጡ ቀጠሮዎች ምክንያታቸውና የተከራካሪ ወገኖች አለመቅረብ የሚያስከትለው ውጤት በኢትዮጵያ የፍትሐብሄር ሥነ-ሥርዓት ሕግ፡- ሕጉና አተገባበሩ. Hawassa University Journal of Law, 5. Retrieved from https://journals.hu.edu.et/hu-journals/index.php/hujl/article/view/419